News Detail

National News
Oct 26, 2020 1.4K views

ሚኒስትሩ በ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፊዚክስ ትምህርትን ለ12ኛ ክፍል ማስተማር ጀመሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ( ፒ ኤች ዲ) የመምህራንን ጫና ለመቀነስ እኔም አስተምራለሁ የሚለውን ንቅናቄ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማስተማር ጀምረዋል።

ሚኒስትሩ በሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፊዚክስ ትምህርትን አስተምረዋል።።

በትምህርት ቤቱ በሚወጣ መርሃ ግብር መሰረትም ለ45 ቀን የማስተማር ስራውን እንደሚከውኑ ገልፀዋል።

ሌሎችም በመምህርነት ሙያ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በመምህራን ላይ የሚኖረውን ጫና ለመቀነስ በበጎ ፍቃደኝነት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁን ሰዓት በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጀምረዋል።

Recent News
Follow Us