News Detail
Oct 24, 2020
819 views
ሙያ ያላቸውና ስራ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራት የተለያዩ አሰራሮችን እየዘረጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኔዘርላንድ ኢምባሲ ያዘጋጀው "Youth at heart" የተሰኘ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ዝግጅት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ተቋማቸው እያከናወናእውን ያለውን አዳዲስ ስራዎች የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሙያ ያላቸውና ስራ መፍጠር የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራት ከመደበኛ ትምህርት ጎን ለጎን የሙያ ትምህርት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ትምህርትን ያልተማከለ ለማድረግም ትምህርት ሚኒስቴር በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ወጣቶች ተሞክሯቸውንና በስራቸውን ያጋጠሟቸውን ችግሮች ያቀረቡ ሲሆን ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሮግራሙ በየአመቱ ኔዘርላንድ ውስጥ ይካሄድ የነበረ ሲሆን በኮቪድ 19 ምክንያት በየ ሀገራቱ የሚገኙ የኔዘርላንድ ኢምባሲዎች እንዲያዘጋጁት ተደርጓል።