News Detail
Jul 22, 2025
78 views
"ለትውልድ ስንል አረንጎዴ አሻራችንን ያለልዩነት እናስቀምጣለን" የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ
የትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ አካሄዱ።
"በመትከል ማንሠራራት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የአረንጎዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉት የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ሮ ብርሃኑ ነጋ ለትውልድ ስንል አረንጓዴ አሻራችንን ያለልዩነት እናስቀምጣለን ብለዋል።
ሚንስትሩ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ባስተላለፉት መልእክት ሀገርና ትውልድን በሚጠቅሙ ጉዳዬች ላይ ሁሉም ዜጋ ያለልዩነት የበኩሉን አስተዋጾ ማድረግ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተከናወነው የችግኝ ተከላ ከስራና ሙያ ጋር የተያዘና ለተማሪዎች አርያ ለመሆን ታስቦ መሆኑን የገለጹትት ሚንስትሩ ሁሉም ዜጋ ባለው የሙያም ይሁን ማህበራዊ ትስስር ሁሌም አረንጓዴ አሻራውን ማኖር አለበት ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ሀገራችን እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ሌሎች ሀገራት ልምድ የሚቀስሙበት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ልማቱ የተፈጥሮ ሚዛንን ከማስጠበቅ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጭምር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ለጋዜጠኞች በሠጡት ማብራሪያ ገልጸዋል።
አረንጓዴ አሻራን ማኖር አገራችን ኢትዮጵያን ወደፊት የሚወስድና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዋነኛ ተግባር በመሆኑ የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ሚንስትር ዴኤታዋ አያይዘው ገልጸዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለትውልድ ምቹና ተስማሚ ሀገር ለማስረከብ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።
መርሃ ግብሩ የአረንጎዴ አሻራ የሁሉም ነገር መሠረት ስለመሆኑ እንዲሁም አገርን ለማበልጸግና ወደፊት ለማሻገር ቁልፍ ሚና ያለው ስለመሆኑ ግንዛቤ የተፈጠረበት ነው።
በመርሐ ግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የኢትዮጵይ ትምህርት ባለስልጣን እንዲሁም የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
Recent News
Jul 11, 2025