News Detail

National News
Jul 01, 2025 60 views

ዩኒቨርሲቲዎች የተሠጣቸውን ተልዕኮ በሚገባ ለይተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ጊዜ ከተከፈቱ ተጠያቂነት የለም ማለት አይደለም፦ በተሠጠው ተልዕኮ መሠረት ካልሰሩ የተጠያቂነት ሥርዓት ሊዘረጋ ይገባል ብለዋል።
በተለይም ዩኒቨርሲቲዎች በእውነትና እውቀት ለሀገር የሚጠቅም ውይይት የሚደረግባቸው፣ ብቃት ያላቸው የሰው ሃይል ማፍራት የሚችሉ ትክክለኛ ዩኒቨርሳል የሆነ አቋም ሊኖራቸው ይገባል ለዚህም ትኩረት ተሠጥቶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስት ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች አለም አቀፍ እውቀት የሚገበይባቸው ተቋማት በመሆናቸው ተቋማዊ አሰራርን መዘርጋት ተገቢ ነው ለዚህም የዩኒቨርስቲ አመራር ምደባ በእውቀትና በአለም አቀፍ ውድድሮች ሊሆን ይገባል ያሉ ሲሆን
እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚሰራው ሥራ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በዩኒቨርቲው በተደረገው የሱፐርቪዥን ግኝት መሠረት ሪፖርት ያቀረቡት የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንደር አስተሳሰብ ወጥተው እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
አያይዘውም ዩኒቨርሲቲዎች በእውቀት መመራት መቻል አለባቸው ለዚህም ተቋማቱን ሪፎርም የማድረግ ሥራ እየተሰራ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
አዲሱ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲውን የተሻለ ተወዳዳሪ ለማድረግ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ጋር በመወያየት አቅደው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላትም ከአካዳሚክ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተው በከፍተኛ አመራሮቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
Recent News
Follow Us