News Detail
Jun 27, 2025
24 views
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁልፍ የሪፎርም ስራዎች አተገባበርና አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ጉባኤ ተካሄደ።
"አካዳሚያዊ ውይይት ለአካዳሚክ ልህቀት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ጉባኤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዘዳንቶችና የአካዳሚክ ፕሮግራም ሀላፊዎች በቁልፍ የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምና አሁን ላይ ያሉበትን ደረጃ በተመለከተ ልምዳቸውን አጋርተዋል።
በትኩረትና ተልኮ መስክ ልየታ (differentiation) ፤ በሥርዓተ ትምህርት ክለሳ( Curriculum revision)፤በሠራተኞችና ተማሪዎች የሙያ እድገት (Staff and students career development)፤ በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካች መነሻና ኢላማ ልየታ ፤ KPI baseline and target identification),፣ የአፈጻጸም ኮንትራት ውል (Performance contracting implementation ) እንዲሁም በብሄራዊ ፈተናዎች አስተዳደርና አፈጻጸም ላይ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸው ተቋማት ልምድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በቀረቡት ተሞክሮዎች ላይ ሀሳባቸውን ያካፈሉት በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሜጄና አንዳንድ ተቋማት የሄዱበትን እርቀት አበረታተዋል።
ይሁን እንጂ በተወሠኑ ተቋማት ያለው ወጥነትና ቁርጠኝነት በሚፈለገው ልክ ባለመሆኑ ተቋማቱንም ይሁን የተቋማቱን ስራ ሀላፊዎች ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ዴስክ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ነገዎ በበኩላቸው ባቀረቡት የስራ ሪፓርት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያከናውኑት የለውጥ ስራዎች ምቹ መደላድል የተፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል።
አክለውም የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ እንዲሁም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ማፍራት የሚቻለው በየደረጃው ያለው የትምህርት መዋቅር ሀላፊነቱን በሚገባ ሲወጣ በመሆኑ እዚህ ላይ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች ስር የሚገኙ የስራ ክፍሎች አፈጻጸማቸውንና ያከናወኗቸው ዋና ዋና ተግባራትን ለጉባኤው አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመድረኩም በ2018 የትምህርት ዘመን በትኩረት መከናወን በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባኤው ተጠናቋል።