News Detail

National News
Jun 29, 2025 17 views

ሚኒስቴሩ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ የሚያስገነባው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ።

የትምህርት ቤቱን ግንባታ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ትምህርት ቤት በአርብቶ አደር አካባቢ የሚገነባ መሆኑን በመጥቀስ እያንዳዱ የኢትዮጵያ ልጅ እኩል የትምህር እድል እንዲያገኝ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
ሁሉም ዜጎች አኩል እድል አግኝተው የሚማሩበት እና የበቁ፣ ተወዳዳሪ የሆኑ ልጆችን ለማፍራት በሁሉም ቦታ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይጠበቃልም ብለዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማው ዘውዴ በበኩላቸው የዚህ ትምህርት ቤት ግንባታ ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ትምህርት ቤቱ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እንደ ልህቀት ማዕከል ይሆናል ያሉ ሲሆን ለአርብቶ አደሩ ልጆ ትልቅ የተስፋ መሰላል በመሆኑ ለግንባታው መጠናቀቅ አስፈለጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፈን ሲሆን 537 ሚሊየን ብር ይፈጃልም ተብሏል።
ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ይህ ትምህርት ቤት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ወላጆች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ በመድረኩ ተጠይቋል።
ግንባታው ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅም በትምህርት ሚኒስቴርና በክልሉ ትምህርት ቢሮ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።
Recent News
Follow Us