News Detail

National News
Jun 25, 2025 18 views

የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሻሪፍ ሚያን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ወቅት ሁለቱ አካላት በትምህርቱ ዘርፉ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዘሪያ ውይይት አድርገዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም ለአምባሳደሩ ካብራሩ በኋላ የፓኪስታንን የትምህርት ሥርዓት እንደሚያውቁ ጠቅሰው በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ፣ በአጠቃላት ትምህርት መምህራን ስልጠና እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ከፓኪስታን ጋር በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ አንስተውላቸዋል።
በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሻሪፍ ሚያን በበኩላቸው ፓኪስታን በትምህርቱ ዘርፉ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
በተለይም ፓኪስታን በመምህራን ስልጠና፣ በሥርዓተ ትምህርት ልማት፣ በሀገራዊና እና አለም አቀፋዊ ስታንዳርድ የፈተና ዝግጅት እንዲሁም በፕሮፌሽናል ትምህርት የተሻለ ተሞክሮ እንዳላት በመጥቀስ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልበትን ሁኔታ አንስተዋል።
ሁለቱ አካላት በነበራቸው ውይይት በትምህርቱ ዘርፍ እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በጋር ለመስራት ተስማምተዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት በሁለቱ አካላት መካከል በከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራም ፣ በአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በህክምና ትምህርት መስክ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ከስምምነት መደረሳቸውም በመድረኩ ተገልጿል።
Recent News
Follow Us