News Detail

National News
Sep 21, 2020 475 views

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በአግባቡ በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

ሚኒስትሯ ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ነው፡፡

ትምህርት ለመጀመር ከመወሰኑ በፊት ግን ጠንካራ ግብረ ኃይል በየደረጃው ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ መርቷል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበር ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ጥናቶችን እያካሄደ መሆኑ ይታወሳል፡፡

Recent News
Follow Us