News Detail
Dec 25, 2024
41 views
በማዕከላዊ ቀጠና ስር የተመደበው የኦሮምያ ብሄራዊ ክልል የተማሪዎች የስፖርት ሊግን አስጀመረ።
በኦሮምያ ክልል የትምህርት ቤቶች የስፖርት ሊግ ውድድር በአዳማ ከተማ በስምንት የመንግስት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካሄድ ጀምሯል።
ስፖርትዊ ውድድሩ የክልሉና የአዳማ ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
ውድድሮቹ የተጀመሩት በእግር ኳስ፣ በቮሊቦል እና በአትሌቲክስ ስፖርት አይነቶች ሲሆን በሁሉም ውድድሮች በርካታ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የስፖርት ውድድሩ ተማሪዎች ያላቸውን መልካም ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ በአካልና በአእምሮ እንዲሁም ሁለንተናዊ ስብዕና የተላበሱ ቀልጣፋ ዜጋ እንዲሆኑ እንደሚያደርጋቸው በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ተገልጿል።
በተጨማሪም ስፖርታዊ ውድድሩ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሳለጥ የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ትልቅ ሚናና ድርሻ እንዳለው በማመን ወደ ስራ የተገባ መሆኑም ተገልጿል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የተማሪዎች የስፖርት ውድድር በተለያዩ የምድብ ቀጠናዎች እየተካሄደ ይገኛል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024