News Detail
Nov 22, 2024
94 views
የአውሮፓ ህብረት ERASMUS+ የትምህርትና ስልጠና ደጋፍና ትብብር አሰጣጥን አስመልክቶ ውይይት ተደረገ፡፡
የመረጃ ልውውጡ የአውሮፓ ህብረት በትምህርትና ስልጠና የሚሰጣቸውን ድጋፎች አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የከፍኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት የአውሮፓ ህብረት በ “ERASMUS+” የትምህርትና ስልጠና ድጋፍና ትብብር እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
መስል ድጋፎችና ትብብሮች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም ከመገንባትና አለም አቀፍ ትብብርን ከማሳደግ አኳያ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ የሚገኙ እድሎችን አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ ሚንስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትጵያ አምባሳደር ሆነው የተሰየሙት ክብርት ሶፊ ፍሮም ኤምስበርገር በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም ለ650 ያህል ኢትዮጵያውን የነጻ ትምህርት እድል የሰጠ መሆኑን በመጥቀስ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና በበኩላቸው መሰል ድጋፎችና ትብብሮች የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉን አቅም በመገንባት ረገድ በሚኖራቸው ፋይዳ ላይ ሠፊ ገለጻ አድርገዋል።
መርሃ ግብሩን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በበይነ መረብ ጭምር ታድመውታል፡፡