News Detail

National News
Jul 19, 2024 2.2K views

የ2016 ዓ. ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በሠላም መጠናቀቁ ተገለፀ።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በመላ ሀገሪቱ በወረቀትና በኦላይን ሲሰጥ የነበረው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ገልፀዋል።
በዚህም ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት 701,749 ተማሪዎች ውስጥ 684,372 ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ ፈተናው በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጻኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። ሙሉ መግለጫውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ። rb.gy/u17yql
Recent News
Follow Us