News Detail

National News
Jun 29, 2024 812 views

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች "ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሻለ ሃገራዊ ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ዉይይት አደረጉ።

ተረጅነትና የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን በመቀነስና የውስጥ አቅምን በመገንባት ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነትን ማስከበር እንደሚገባ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በውይይቱ ማስጀመሪያ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገራችን በርካታ ተፈጥሯዊ እና የሰው ሀብት ዕምቅ ፀጋ ያላት ባለታሪክና ገናና ሀገር ሆና ሳለ የድህነት ተምሳሌት መሆኗ ሁላችንንም ላይ ቁጭት ሊፈትጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ክቡር ሚንስትር ዴኤታው አክለው እንደገለጹት ሁሉም ዜጋ ከተረጅነት አመለካከት ወጥቶ በቁርጠኝነት በመስራት በህብረተሰቡ ላይ ሊከሰቱ ለሚችሉ አደጋዎች ተገቢ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይልቃል ወንድሜነህ በበኩላቸው ሠነዱን አስመልክቶ ባደረጉት ገለጻ ሰባዊ ድጋፍ እና የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የመንግስት ድርሻ ብቻ አለመሆኑን ገልጸው ለዚህ ስኬታማነት ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አብራርተዋ።
መንግስት የተለያዩ የቅድመ አደጋ መከላከል ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑም በሰነዱ የተገለፀ ሲሆን እያንዳንዱ ዜጋም ያሉትን መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም በቅንጅት ለውጤት ተኮር ተግባራት መዘጋጀት እንዳለበትም አክለው ገልጸዋል።
የሃገር ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዘርፉን በተመለከተ የተቀናጀ የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂ ተነድፎ ሁሉም ሰራተኛ የስራዉ ዕቅድ አካል አድርጎ የሚሰራበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚገባ በማጠቃለያው ላይ ተገልጿል።
Recent News
Follow Us