News Detail
Jul 07, 2024
1K views
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ:- ከሐሰተኛ ወሬዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ ስለማስገንዘብ!
የትምህርት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በበይነ መረብ (ኦንላይን) እና በወረቀት ለመፈተን ዝግጅቱን አጠናቅቆ የተማሪዎችን የመፈተኛ ቀን እየተጠባበቀ ይገኛል።
ነገር ግን ፈተናውን አስመልክቶ የተሳሳቱ መልዕክቶች በየጊዜው ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር ባልሆኑ ገጾች እየተለቀቁ ይገኛሉ።
ስለሆነም ተማሪዎች፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ፈተናው ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው በበይነ መረብና በወረቀት እንደተማሪዎች #የቀደመ ምርጫ መሰረት የሚካሄድ መሆኑን በመገንዘብ አስቀድማችሁ በወረቀት የመረጣችሁ ወደተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ፣ በበይነ መረብ የመረጣችሁም በተመደባችሁበት የፈተና ጣቢያ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንደምትወስዱ ለማስገንዘብ ይሄንን መልዕክት እናስተላልፋለን።
ውድ ተማሪዎች በምስሉ ላይ ከተገለጹት አይነት ሃሰተኛ ወሬዎች ራሳችሁን በመከላከል ለፈተናው የምታደርጉትን ዝግጅት እንድትቀጥሉ እያሳሰብን ለማንኛውም መረጃ የሚከተሉትን የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ ገጾች ብቻ እንድትከተሉ እናሳስባለን።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024