News Detail
Jun 27, 2024
6K views
የ2016ዓ.ም የፋርማሲ የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ለተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ. ም በ 244 ፕሮግራሞች በ57 የመንግስትና በ124 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ለስድስት ቀናት የተሰጠው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የተሰጠዉ የፋርማሲ ፈተና ብቻ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል። ስለሆነው ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ፈተናውን በድጋሜ እንዲወስዱ አመቻችቷል።
በዚሁ መሰረት ፈተናው በድጋሜ ቅዳሜ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከ 3:00 ሰአት ጀምሮ እና ከሰአት ከ 8:00 ሰአት ጀምሮ ስለሚሰጥ ለፈተናው ተቀምጣችሁ የነበራችሁ የፋርማሲ ተማሪዎች በተፈተናችሁበት የፈተና ጣቢያ በሰዓቱ በመገኘት በድጋሜ የሚሰጠውን ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026