News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
May 21, 2026 56 views

በፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የሚመሩት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በለንደኑ ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2026 በመሳተፍ ላይ ነው፤

በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በለንደን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የትምህርት ፎረም (World Education Forum 2026) ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
የዘንድሮው ፎረም "ለጋራ የወደፊት ጊዜ ትምህርት መስጠት፡ ሰላም፣ ፕላኔት፣ ዓላማ እና መንገዶች በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ይህ መድረክ በዓለም አቀፍ ደረጃ በትልቁ የሚጠቀስ የትምህርት እና የክህሎት ሚኒስትሮች ስብሰባ ነው።
በዚህ ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም ላይ ከመላው ዓለም የመጡ ሚኒስትሮችን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እና የትምህርት ቴክኖሎጂ መሪዎችን በአጠቃላይ ከ125 አገሮች የመጡ ከ1500 በላይ የሚኒስትሮች የልኡካን ቡድን ተገኝተዋል።
ይህ ታላቅ ፎረም ሚኒስትሮች እና የትምህርት መሪዎች የፖሊሲ ልምዶችን እንዲለዋወጡ፣ አዳዲስ ስልታዊ አጋርነቶችን እንዲፈጥሩ፣ በትምህርት ፋይናንስ እና ማሻሻያዎች ላይ እንዲወያዩ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ትምህርትን ቀጣይ አቅጣጫ ለመቅረጽ ከፍተኛ ዕድል የሚፈጥር መድረክ መሆኑም ተመላክቷል።
ልዑካን ቡድኑ በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያን የትምህርት ሪፎርም እና ተሞክሮዎች ያካፈለ ሲሆን፣ በቀጣይ የሀገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል በሚረዱ ዋና ዋና ዘርፎች ላይ ውይይቶችን አድርጓል።
በዚህ መድረክ ሀገራችን ያላትን ልምድ ያካፈለች ሲሆን በመሠረታዊ ትምህርት፣ በቅድመ ልጅነት እድገት፣ በመምህራን ስልጠና፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በወጣቶች ክህሎት ልማት ላይ ከተለያዩ አገሮች ልምድ ለመቀስም ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑ ተጠቅሷል።
Recent News
Follow Us