News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
May 21, 2026 43 views

ኢትዮጵያ በለንደን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2026 በትምህርቱ ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ አካፈለች፤

ኢትዮጵያ በለንደን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የትምህርት ፎረም 2026 ላይ ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ጥራት ያለው የትምህርት ሥርዓት በመገንባት ረገድ ያላትን ልምድ አቅርባለች።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ በትምህርት ተደራሽነት፣ አካታችነት እና የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዙሪያ ያከናወነቻቸውን ተግባራት አብራርተዋል።
በዚህም፦
✅ በገጠርና አገልግሎት በማይደርስባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋት፣
✅ የቅድመ ልጅነት እድገት (ECD) እና የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማጠናከር የተወሰዱ እርምጃዎች፣
✅ የአካል ጉዳተኞችንና የልዩ ትምህርት ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የሚደግፉ አካታች ፖሊሲዎችን መተግበር፣
✅ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎችን ተሳትፎና መሰረታዊ ትምህርት ማሻሻል፣
✅ የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ እና ቆይታ ለማሳደግ የተሰሩ ሥራዎች፣
✅ ለአርብቶ አደርና ለመድረስ አስቸጋሪ ማህበረሰቦች አማራጭ የትምህርት ፕሮግራሞችን መተግበር፣
✅ የትምህርት ጥራትን፣ ፍትሃዊነትንና አካታችነትን ለማጠናከር የመምህራን ልማትን ማበረታታት የሚሉ ቁልፍ ተሞክሮዎች አቅርባዋል።
በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎች ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት እንደገና አረጋግጣለች።
በተጨማሪም ክቡር ሚኒስትሩ ጎን ለጎን በተካሄደው የአፍሪካ ትምህርት ሚኒስትሮች መድረክ ላይ “በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል” ንቅናቄ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ ሰፊ የትምህርት ልማት ተግባራትን በማቅረብ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍለዋል።
Recent News
Follow Us