News Detail

National News
Jun 04, 2024 3K views

ተማሪዎች በበይነ መረብ (Online) መፈተናቸው ምን የተለየ ጠቀሜታ አለው?

1. የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም
ይህም ለምሳሌ በወረቀት መልስን በማጥቆር ሂደት ተማሪዎች መልስ ሳይሰጡ ሊያልፉና ሊረሱ የሚችሉበት ወይም በመልስ ቅየራ ወቅት የመልስ መስጫ ወረቀት መጎዳት፣ ሁለት መልስ መጻፍ፣ አጋጣሚዎች ሲኖሩ እንዲሁም ከአንዱ ጥያቄ ወደ ሌላኛው ለማለፍ ገጽ ማገላበጥ ወ.ዘ.ተ. ሲኖርባቸው፣ በበይነ መረብ ሲሆን ግን ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንዳሉ የሚጠቁም በመሆኑ፣ አንዱን ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ “click” የመሄድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ “flag” በማድረግ ተመልሶ የመስራት እድልን ይሰጣል።
2. ጊዜ ቆጣቢ ነዉ፡፡
ወረቀት ላይ መልስ በማጥቆር የሚባክን ጊዜን በማስቀረት በአንድ “click” የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያነሳሳል።
3. የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው፡
የበይነ መረብ ፈተናዎች፡ በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ፈተና ተማሪዎች ከሚፈተኑበት አከባቢ አንጻር በ5 ክላስተሮች በመመደብ፤ 5 ወደ ፈተና መግቢያ ማስፈንጠሪያ (URL) ተዘጋጅቷል። ማስፈንጠሪያው የተለያየ የሆነበት ምክንያት በፈተና ወቅት ያለውን የኢንተርኔት መጨናነቅ ለመቀነስ እንጂ በተሰጠው ሊንክ የገባ ማንኛውም ክልል እና ከተማ ላይ ያለ ተማሪ የሚገባበት የፈተና ቋት በሌላ ማስፈንጠሪያ ከገባ ተማሪ ጋር ተመሳሳይ ነው።
4. ኦዉቶማቲካሊ የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በራሱ ይልካል፡፡
በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ አውቶማቲካሊ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ ይልካል (ሰብሚት ያደርጋል) ።
5. ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
ፈጣን የውጤት አሰጣጥ እና ግብረመልስ፡ በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ እድል ይኖረዋል።
6. ተማሪዎች በቤታቸዉ እያደሩ እንዲፈተኑ እድል ይሰጣል፡፡
ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ እድል ይፈጥራል።
Recent News
Follow Us