News Detail

National News
Feb 29, 2024 1.4K views

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ሁነቶች አከበሩ፡፡

«ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!»በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ128ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞችና አመራሮች ሰንደቅ አላማ በጋራ በመስቀልና ሊሎች መርሃግብሮች አክብረዋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ችቦ እና አርማ በመሆኑ የድሉን እሴቶችና ቱሩፋቶች በሚገባ ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንደሃገር የዓድዋ ድል መታሰቢያ የሆነው አድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ተጠናቆ በተመረቀበት የሚከበር በመሆኑ ድሉን ድርብ ያደርገዋልም ብለዋል
ሰንደቅ ዓላማ በጋራ የመስቀል መርሃ ግብሩን ተከትሎ በማህበራዊ ሳይንስ ስርዓተ ትምህርት ሃላፊ አቶ ኡመር ኢማም የውይይት መነሻ ያቀረቡ ሲሆን የህዝቦች አብሮ የመኖርና የመልማት እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳዮች ላይ ይህ ትውልድ ከአባቶቹ ብዙ መማር እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡
በውይይቱ የማጣቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊው አቶ ጌታቸው ተፈራ በበኩላቸው የአድዋ ድል ቀደምት አባቶቻችን ብሄራቸው፣ ቋንቋቸው፣ ሀይማኖታቸው፣ባህላቸውና ሌሎች ልዩነቶቻቸው ሳይገድባቸው የሀገርን ሉዓላዊነትና አንድነት በማስከበር ያቆዩን መሆኑን አብራርተው አሁን ያለው ትውልድ ከዚህ መማር እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
Recent News
Follow Us