News Detail
Jan 27, 2022
1.3K views
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በአማራና አፋር ክልሎች 4 ትምህርት ቤቶችን ለያስገነባ ነው።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራት ትረስት ፈንድ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት 3 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተመደበ ሲሆን በአንድ አመት ውስጥ ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናሉ ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው ሁለቱ ክልሎች ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ላደረገው አጋርነት አመስግነዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የሚያስገነባቸውን ትምህርት ቤቶች ጨምሮ በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገነቡት ትምህርት ቤቶች ከቀድሞውም በተሻለ መልኩ ደረጃቸውን ጠብቀው ይገነባሉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያያ ዲያስፖራ ትረስ ፈንድ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገብርኤል ንጋቱ ትረስ ፈንዱ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው ሁለቱ ክልሎች የሚያስገነባቸው አራት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲገነቡ ተገቢውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ፈንዱ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ሁለቱ ክልሎች በተጨማሪ ጦርነቱ ሲያበቃ በትግራይ ክልልም ትምህርት ቤቶችን የመገንባት ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል።