News Detail
Jan 21, 2022
1.8K views
በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው።
ትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱና በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ናቸው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል።
ትምህርት ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበ፣ት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውንም ተናግረዋል።
በትምህርት ቤቶቹ የ 8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ናቸው።
በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ይሆናሉ።
Recent News
የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
Feb 27, 2026
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
Feb 13, 2026