News Detail
ዲያስፖራው የኢንተርኔት ግንኙነት በሌለበት ቦታ የዲጂታል ትምህርት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለሙከራ ይዘው መጡ
አቶ ሚደቅሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
በዚህም መሰረት ወደ ሀገር ሲመጡ የኢንተርኔት ግንኙነት የሌላቸው ትምህርት ቤቶችን ሊጠቅም የሚችል ቴክኖሎጂ ይዘው እንደመጡ ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው በሶላር ሃይል የሚሰራ፣ የራሱ ዋይፋይ ያለውና ተንቀሳቃሽ 2 ቴራባይት ሰርቨር የያዘ ሲሆን ከኮምፒውተርና ከሞባይል ጋር በማገናኘት የመማሪያ መሳሪያዎችን ማግኘት የሚቻልበት ነው።
ቴክኖሎጂው የተለያዩ የትምህርት አይነቶች የያዙ መፅሃፍት፣ መርጃ መፅሃፍት፣ ሌክቸሮችና ቪዲዮዎች፣ ጥናታዊ ፅሁፎች፣ ንግግሮች፣ መዝናኛዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎችንም ማስረጃዎች የሚይዝ ነው።
ከ60 ሺ በላይ መፀሃፍትን የያዘው ስርዓቱ መፅሃፍቶቹን በማንኛውም ጊዜ በነፃ ማውረድም ያስችላል።
በአሁን ሰዓት መሳሪያውን በሀገር ውስጥ ለመጠቀም እንዲቻል የትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ ባለሙያዎች እንዲገመግሙት እየተደረገ ነው።
ባለሙያዎቹ ሲስተሙ ላይ የሀገር ውስጥ የትምህርት አይነቶችን በመጫን ሀገርኛ ይዘት እንዲኖረው የማድረግ ስራዎችን እንደሚሰሩም ተገልጿል።በቀጣይ የዚህን ቴክኖሎጂ ውጤታማነት ተገምግሞ ቀጣይ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።
ሌሎች ትውልደ ኢትዮጵያውያንም ወደ ሀገር ሲመጡ የትምህርት ስርዓቱን ሊያግዝ የሚችል ድጋፍ እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስቴር ጠይቋል።