News Detail

National News
Jan 03, 2022 288 views

በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ትምህርት ተጀምሯል።

በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ከሁለት ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ ተጀምሯል።

በሁለቱም ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።

የሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ያሬድ ጌታቸው በአሸባሪው ህውሓት ወረራ ምክንያት ሁለት ወር ከ15 ቀን በኃላ በድጋሜ ትምህርት መጀመሩን ገልፀዋል።

ትምህርት ቤቶቹም ባለው ግብዕት መደበኛ  የመማር ማስተማር ሂደትን እያስቀጠሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ከ70% በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም በትምህርት ቤቶች ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

Recent News
Follow Us