News Detail
Nov 24, 2021
449 views
በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲከተቡ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
የትምህርት ሚኒስቴር ከ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮቪድ_19 ክትባት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል።
የጤና ሚኒስቴር በትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ 12 ዓመት በላይ ለሆኑ ህፃናት የኮቪድ-19 ክትባትን እየሰጠ ነው ።
ነገር ግን በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ በሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት የቤተሰቦች ፍቃደኝነት አናሳ መሆኑ ተስተውሏል።
ይህንን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀረጓ ማሞ በትምህርት ቤቶች የሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት በተፈለገው ደረጃ እንዲደርስ የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
ስለዚህም ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚሰጠውን ክትባት እንዲወስዱ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።
በትምህርት ቤቶች እየተሰጠ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት በትምህርት ዘርፉ ላይ ሊከሰት የሚችለውን የኮቪድ-19 ስርጭት እንደሚቀንሰውም ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ክትባት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመቻ መልክ እየተሰጠ ይገኛል።