News Detail

National News
Nov 23, 2021 287 views

አገር አቀፍ የትምህርት ዘርፍ አማካሪ ምክር ቤት ተቋቋመ

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የአማካሪ ምክር ቤቱ መቋቋም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት እንደ አገር የትምህርት ጥራት ያሉበትን ችግሮች ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት ያስችላል ብለዋል፡፡
አማካሪ ምክር ቤቱ በትምህርት ጥራት ላይ የሚደረጉ ሀሳቦችን በሙያዊ ዓይን እየገመገመ እና በሴክተሩ የሚሰሩ ስራዎችን እየተከታተለ ከሙያ አንጻር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የማማከር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የአማካሪ ምክር ቤቱ በንዑሳን ዘርፎች በውስጥ የሚደራጅ ሆኖ ለጊዜው 20 አባላት የሚኖሩት ይሆናል፡፡
ምክር ቤቱ ሰፊ ልምድ ያካበቱና በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ምሁራን የተካተቱበት እንደሆነም ተገልጿል።
የምክር ቤቱ አባላት ቀጣይ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍና ከፍተኛ ትምህርት በንኡሳን የለውጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን በማማከር ለአገራችን የትምህርት ጥራት መጠበቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Recent News
Follow Us