News Detail
Nov 23, 2021
286 views
የትምህርት ሚኒስቴር በ አፍሪካ ደረጃ የሚተገበረውን ሀገር አቀፍ የ ትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም መመሪያ እየገመገመ ይገኛል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ውጤታማነት ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ መመሪያውን እየገመገመ ይገኛል፡፡
መድረኩ በሀገር አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ መመሪያ ላይ ውይይት በማድረግ ግብዕት ለመሰብሰብ ያለመ ነው።
በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ዬሀንስ ወጋሶ የትምህርት ቤት ምገባ በትምህርት ቤቶች እንዲተገበር መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን እና መመሪያውንም ወጥ እና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመድረኩም የትምህር ቤት ምገባ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ደሊል ከድር አጠቃላይ በአፍሪካ ደረጃ የሚተገበረውን ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መመሪያ ላይ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ያደረጉ ሲሆን በአጠቃላይ ዝርዝር ሰነዱ ላይ አቶ መኳንንት ዳኘው ገለፃ ሰጥተው ውይይት ተካሂዶበታል።
የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መመሪያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ55ቱም የአፍሪካ ሀገራት ወጥነት ባለው መልኩ ለመተግበር የሚያስችል ነው ተብሏል።
የሀገር በቀል ትምህርት ቤት ምገባ የትምህርትን ተደራሽነትና ጥራት ለማሻሻል የአፍሪካ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ቀጠናዊ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ይህን በ አፍሪካ ደረጃ የሚተገበረውን ሀገር አቀፍ የትምህርት ቤት ምገባ መመሪያ እንዲገመግሙ ከተመረጡ 16 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዬጵያ አንዷ ነች።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024