News Detail
Oct 26, 2021
266 views
የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቃት ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
የትሞህርት ሚኒስቴር ከኢዲቲ ጋር በመተባበር የትምህርት ቤት የአመራሮችን አቅም ለመገንባት በምዘና ለተመረጡ የዩኒቨርስቲና ኮሌጅ መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን ልማትና አስተዳደር ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ሞረዳ የትምህርት ዘርፉ የሰው ኃይል አቅም ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የትምህርት ዘርፉ የሰው ኃይል አመራር ከዘርፉ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲሁም ከሚፈለገው ለውጥ አንጻር የተመጣጠነ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የርዕሰመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን ብቃት ማሳደግ ትምህርት ቤቶችን በማሻሻል የለውጥ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል ።
የኢዲቲ ዳይሬክተር ዶክተር አብዱ ዘለቀ በበኩላቸው ስልጠናው የትምህርት ቤት አመራሮችን ክህሎትና የአመራርነት አቅም ከማጎልበት ባሻገር የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል እንደሚረዳም ተናግረዋል።
በቀጥይ ስልጠናው ትምህርት ቤት አመራሮችም እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024