News Detail

National News
Oct 06, 2021 586 views

በ2014 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ፅዱ በማድረግ ኮሮናንና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ጥሪ ቀረበ።

የዓለም የጽዳት ቀን “ ንጹህና ጽዱ ትምህርት ቤት ለትውልድ “ በሚል መሪ ቃል በመነን ት/ቤት ተከብሯል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) በ2014 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን ጽዱ በማድረግ የኮቪድ 19 በሽታን ለመከላከል ስራ የሚሰራበት ዓመት ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባና በሁሉም የከተማና የክልል መስተዳድሮች በየደረጃው ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ርዕሰ መምህራን ፣ መምህራን እና ተማሪዎች በትምህርት ዘመኑ ትምህርት ቤቶቻቸውን ፅዱ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ሚኒስተሯ ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በትምህርት ቤቶች ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎችን በአግባቡ በማስወገድ ኮሮናና ሌሎችም በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎችን በመከላከል ለሌሎች ምሳሌ መሆን እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ዛሬ በትምህርት ቤቶች የተጀመረው የንቅናቄ ፕሮግራም በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስኬታማ በማድረግ ንጹህ ትምህርት ቤቶችንና ንጹህ አካባቢዎችን በመፍጠር ንጹህ አዲስ አበባን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
Recent News
Follow Us