News Detail
Oct 06, 2021
581 views
ትምህርት ሚኒስቴር ለየህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄደ፡፡
መርሃ ግብሩ የተካሄደው የቋሚ ኮሚቴው አባላት አጠቃለይ ትምህርት ዘርፉ አሁን ላለበት ደረጃ መድረስ ላደረጉት አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ነው።
የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚው አበላት በስራ ዘመናቸው የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉን ችግሮችን በመለየት ፣ በማበረታታትና በመደገፍ መልካም ተግባራትን ማከናወናቸውን የትምህርት ሚኒሰትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የቋሚ ኮሚቴው አባላት በአገልግሎት ዘመናቸው ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን አደራ በአግባቡ በመወጣት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውነን አቅርበዋል።
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እምዬ ቢተው የትምህርት ጉዳይ ትውልድን የመቅረፅ ጉዳይ በመሆኑ የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት ዘርፍ ለቀጣይ የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር በዘርፉ የጀመረውን የሪፎርም ስራ በቀጣይም አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡
በስነ ሰርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን ለቋሚ ኮሚቴው አባላት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024