News Detail
Oct 06, 2021
1.1K views
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ቀድሞ የተማሩባቸውን ትምህርት ቤቶች ጎበኙ፡፡
ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባቦራ ዞን ኡካ ቀበሌ የሀሉ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህር ቤትን በመጎብኝት ለተማሪዎች ንግግር አደገዋል።
በትምህርት ቤቱ ያሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር ሀገራቸውን የሚያገለግሉ ዜጋ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
አለምን እየመሩ ያሉ መሪያዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ ዶክተሮችና ሌሎችም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አልፈው ነው ለስኬት የበቁት ያሉት ሚኒስትሩ ተማሪዎች ውጣ ውረድ ሳያደናቅፋቸው ጠንክረው እንዲማሩ መክረዋል።
የሃሉ የመጀመሪያ ደረጃ እንዲሁም የኡካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች እድሳት ላይም ድጋፍ እንደሚያደረጉ ቃል ገብተዋል።
በጉብኝቱ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣የኦሮምያ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ የዞን አመራሮች እና የአካባቢው ትምህርት ማህበረሰቡ ተሳትፈዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024