News Detail
Jun 16, 2021
765 views
በትምህርት ዘርፍ የሴት አመራርነት ሚናን ማጎልበት ለሴት ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተገለፀ።
የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፍ የሴቶችን አመራርነት ሚና ለማጎልበት ሴት አመራሮች ጥምረት መድረክ ለሁለተኛ ጊዜ አካሄዷል፡፡
መድረኩ የተዘጋጀው Target Ethiopia የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በጋራ በመተባበር ሲሆን በትምርት ዘርፍ ሴቶችን ለአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት የሚያበቃቸውን አቅም ማጎልበትን አላማው ያደረገ ነው።
የትምሀርት ሚነስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ የጥምረት መድረኩ በትምህርት ዘርፍ የሚሰሩ ሥራዎች ዙሪያ ለመወያያትና የጋራ አቋም ለመያዝ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
በትምህርት ዘርፍ የሴት አመራርነት ሚናን ማጎልበት ለሴት ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለውም ገልፀዋል።
ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ወደ አመራርነት እንዲመጡ መንገድ የሚያመቻችና ሌሎች ሴት ኃላፊዎችም የጥምረቱ አባል ባይሆኑም የሕይወት ዘመን ልምዳቸውን የሚያካፈሉበት መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ከኦሮሚያ ክልልና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ የሴት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በቀጣይ በተዋረድ ያሉ ከሁሉም የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተወጣጡ በትምህርት ዘርፍ የሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ 3ኛ የጥምረት መድረክ እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024