News Detail

National News
Jun 20, 2021 1.5K views

በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚኖሩ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች ንቁ ዜጋን ለመፍጠር እንደሚያግዙ ተገለፀ።

ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስፓርት ለሁሉም ዝግጅት ላይ የሚኒስቴሩ አመራሮች እና ሰራተኞች የተለያዩ ስፓርታዊ ውድድሮችን አካሂደዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር ኢንጂ) ስፖርት አካልን በመገንባት ጤናማ ትውልድን ከመፍጠር ባሻገር ንቁ ዜጋን የመፍጠር አቅም ስላለው የዘውትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ንቁና ጤናማ ትውልድን ለማፍራት ስፖርት መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች ትልቅ ሚና ስላላቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በእንግድነት የተገኘው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ ስፖርት አካልን በመገንባትና አዕምሮን በማደስ ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የሚያበረክተው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ የትምህርት ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏል።
ሚኒስቴሩ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ ስፓርታዊ ውድድሮችን በማድረግ ጤናማ እና ንቁ ዜጋን ለመፍጠር እንደሚሰራም አስታውቋል።
በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ጋር የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲስፋፉ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል።
Recent News
Follow Us