News Detail

National News
Oct 06, 2021 598 views

ትምህርት ሚኒስቴር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የጥፋት ቡድኖች ለተጎዱና ለፈረሱ ትምህርት ቤቶች መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር 194 ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ፣ ከ194ቱ ውስጥ 56 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው እና 138 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በከፊል መፍረሳቸው ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጅ)ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ገልፀው ክልሉ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማቋቋም ህፃናትን ወደ ትምህርት ቤት በመመለስ ረገድ ኃላፊነቱ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በ2014ዓ.ም ትምህርት ለማስጀመር በሚደርገው ጥረት በተለያዩ አካባቢዎች በጥፋት ቡድኖች ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች የማቋቋም ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
የገንዘብ ድጋፉን የተረከቡት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ር/መስተዳደር ክቡር አቶ አሻንድሌ ሀሰን በበኩላቸው የህወሃት አሸባሪ ቡድን እና ተላላኪዎቹ በክልሉ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ማድረሳቸውን ገልፀው የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ክልሉ ለሚያደርገው ጥረት ትምህርት ሚኒስቴር ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ክልሉ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባትና ለማቋቋም እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በ አማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መልሶ ማቋቋሚያ የ100 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል፡
Recent News
Follow Us