News Detail

National News
Jan 05, 2021 613 views

ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም ዕሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው፡-ትምህርት ሚኒስቴር

በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ ለመፍጠር ሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ የዜግነትና የሰላም ዕሴቶችን ያካተተ ስርዓተ-ትምህርት ለማዘጋጀት ትምህርት ሚኒስቴር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።

አውደ ጥናቱ በስርዓተ  ትምህርቱ ውስጥ የሀገር በቀል የግብረ-ገብ፣ ዜግነትና የሰላም ዕሴቶች ላይ ግብዓት መሰብሰብ ዓላማ  ያደረገ ነው።

የሚሻሻለው የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት ከ1ኛ -6ኛ ክፍል የግብረ-ገብ ትምህርት እንዲሁም ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ደግሞ የዜግነት ትምህርት ተብሎ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡

ለሚዘጋጀው  የግብረ-ገብና ዜግነት ትምህርት  ስርዓተ ትምህርት  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከወሎ ዩኒቨርስቲ፣ ከአዲስ ኪነ-ጥበባት የባህል ማዕከል፣ ከኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔና ከሌሎች ተቋማት የመጡ ከፍተኛ ምሁራን፣ተመራማሪዎች፣ የፍልስፍናና  የሀይማኖት ሰዎች  ጥናታዊ ፅሁፎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩም ከክልል ትምህርት ቢሮ ፣ ከመምህራን ማህበር፣ ከመምህራን ኮሌጆች፣ ከሰብዓዊ መብት ኮሚሺን፣ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፣ ከሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድረሻ አካለት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

 ከስርዓተ-ትምህርቱ ችግሮች መካከል የግብረ-ገብ ትምህርትን በሚፈለገው ልክ አካቶ አለመያዙ መሰረታዊ  ችግር ሆኖ በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታው ላይ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡

Recent News
Follow Us