News Detail
Dec 30, 2020
547 views
በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የተገነቡ 8 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቀቀ።
በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት የተገነቡ 8 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና አገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስነበበው፤ ትምህርት ቤቶቹ በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኽምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ ናቸው ፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቁ 5 ትምህርት ቤቶችን ማስረከቡ አስታውሷል።
ጽህፈት ቤቱ ትምህርት ቤቶች ከማስገንባት ባለፈ በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል።