News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 06, 2020 384 views

በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚታየው ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳደር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።

ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት በማስቀጠል ሂደት ላይ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ሲያደርጉት የነበረው ምክክር ተጠናቋል።

በምክክር መድረኩ የሃይማኖት አባቶቹ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የመንግስትና የህዝብ ቸልተኝነት እያታየ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ ቸልተኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ስጋታቸውን ገልፀዋል።

መንግስት ኮሮናን ለመከላከል የተቀመጡ መመሪያዎች እንዲተገበሩ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ የጠየቁት የሃይማኖት አባቶቹ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ህብረተሰቡን በማንቃት የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

መንግስት ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል ከማስተማር ባለፈ አስገዳጅ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ተገለጧል።

ተማሪዎችም በትምህርት ቆይታቸውም ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ተብሏል።

Recent News
Follow Us