News Detail
Nov 05, 2020
415 views
ከፌደራል እና ከክልል የተወጣጡ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት በአዲስ አበባ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።
የትምህርት ሚኒስቴር እና ህብረተሰብ ጤና ኢኒሰቲትዬት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፍ የሀይማኖት አባቶች በ አዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ጎበኙ።
የሀይማኖት አባቶቹ ሚኒሊክ መሰናዶ እና ቅደስት ሳላሴ ካቴድራል ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የትምህርት ቤቶቹ ዝግጁነት ምን እንደሚመስል የተመለከቱ ሲሆን በትምህርት ቤቶቹ ውስጥም ትምህርት መጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መደረጋቸውን መመልከታቸውን የሀይማኖት አባቶቹ ተናግረዋል።
የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላቱም በየ አካባቢያቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት ለማስቀጠል በሚደረገው እርብርብ የበኩላቸውን እንደሚወጡ በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል።
ከፌደራል እና ከክልል የተወጣጡ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት በማስቀጠል ሂደት ዙሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውይይት እያካሄዱ መሆኑ ይታወሳል።
የውይይት መድረኩ ነገም የሚቀጥል ይሆናል።