News Detail
Nov 10, 2020
389 views
የትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ፓወር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የተማሪዎች የፈጠራ ስራ ውድድር እየተካሄደ ነው።
የትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ፓወር ጋር በመተባበር ሲያዘጋጀው የነበረው የፈጠራ ውድድር በዛሬው እለት እየተካሄደ ይገኛል።
"የዓለም የሳይንስ ቀን ለሰላም እና ለእድገት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ውድድር በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ ውስጥ ከተለያየ ቦታ የተወጣጡ የፈጠራ ባለሙያዎች ስራቸውን አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ካሪኩለሙን በማሻሻል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግም ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
በዝግጅቱ ላይ በፈጠራ ስራ ዙሪያ የፓናል ውይይት እና የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ተካሂዷል።
የውድድሩ ዓላማ የሳይንስ እና የፈጠራ ስራን በ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለማበረታታት እና ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያወጡ ለማስቻል መሆኑም በዝግጅቱ ላይ ተገልጿል።
የዓለም የሳይንስ ቀን በሀገራችን ለ5ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 18ኛ ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር እና በ ስቲም ፖወር አዘጋጅነት እየተከበረ ይገኛል።