News Detail
Mar 24, 2022
2.1K views
የአፍሪካ ህብረት ሠራተኞች ለወደሙ ትምህርት ተቋማት ከ725 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
የአፍሪካ ህብረት ሰራተኞች በወረራ ምክንያት ለወደሙ ትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ ከ725 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
የተደረገውን ድጋፍም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያና ለትምህርት ሚኒስቴር አስረክበዋል።
የህብረቱ ሰራተኞች ድጋፉን ያደረጉት ከወር ደመወዛቸው ቀንሰው መሆኑም ተገልጿል።
ድጋፉም በአማራና በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ እንደሚውል ነው የተነገረው፡፡
የተደረገው ድጋፍ ቀጣይነት ያለው መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ ትምህርት ቤቶቹ በተሻለ ደረጃ እንዲገነቡ ድጋፉ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልፀዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ ኤሊያስ ግርማ ሰራተኞቹ ስላደረጉት ድጋፍ አመስግነው ገንዘቡ በቀጥታ ለፈረሱ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ እንደሚውልም ተናግረዋል፡፡