News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Mar 24, 2022 2.4K views

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ሊኖር አንደሚገባ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ  ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)  በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሻለ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ሊኖር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመረጃ አቅርቦት የተሻለ ስራ በመስራት ከመረጃ ስርዓት ጋር በተገናኘ ያሉባቸውን ችግሮች ሊቀርፉ እንደሚገባም ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሃላፊዎቹም በተቋማቱ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን እና ተግዳሮቶችን አንስተው ውይይተ ተካሂዷል።

 ከመረጃ አያያዝ ስርዓት ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ፣ ሰላማዊ መማር ማስተማር ማስፈንና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመዋቅር ጥናት ሰነዶች ላይ ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል ፡፡

Recent News
Follow Us