News Detail
Mar 17, 2022
1.4K views
የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ካትሱኪ ሞሪሀራ (ፒ ኤች ዲ) ጋር ተወያይተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ኤጀንሲው በትምህርት ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍም ጠይቀዋል።
የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ ካትሱኪ ሞሪሀራ (ፒ ኤች ዲ) ከ2006 እስከ 2020 እ.ኤ.አ ከ290 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ እንደተደረገና ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶችን መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።
በጦርነት የወደሙና የፈራረሱ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ተቋማቸው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡት ተወካዩ ለትምህርት ቤቶች ከሂሳብና ሳይንስ ትምህርት ጋር በተያያዘ የሚያስፈልጉ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችንና ቁሳቆሶችን እንደሚያሟሉ ገልፀዋል፡፡
የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ከ2003 እስከ 2021 እ.ኤ.አ ድረስ በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡