News Detail
Jul 17, 2020
1.4K views
ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ውጭ ያሉ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ተዛውረው እንዲማሩ ተወሰነ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ውጭ ያሉ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፈተና ተዛውረው በዚህ አመት ያመለጣቸውን ትምህርት እስከ 1 ወር ከ15 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ አካክሰው እንዲማሩ ተወስኗል፡፡
የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ጊዜ ነሃሴ መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ እንደሚጀመር የተገለፀ ሲሆን ከዚህ የጊዜ ሰሌዳ በፊት የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንደማይችሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ተናግረዋል፡፡