News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Aug 31, 2020 647 views

በ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተማሪዎች 12ኛ ክፍልን ሲጨርሱ የሙያ ባለቤት ይሆናሉ። ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ውይይት እያካሄደ ነው ።


በውይይቱ ላይ አጠቃላይ ትምህርት አንዱ የሙያ መማሪያ ዘርፍ እንዲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) በ አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሙያ ትምህርቶችን በሁሉም የሙያ ዘርፎች በመስጠት የተማረ እና በዘርፉ እውቀት ያለው ባለሙያ እንዲፈጠር ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።

ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ሙያ ያለው ተማሪን ለመፍጠር በቀጣይ የሙያ ትምህርቶች ከመደበኛ ትምህርት ጋር በተጣጣመ መልኩ ጎን ለጎን እንደሚሰጥም ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዋች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የሙያ ባለቤት ይሆናሉ ተብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆኑ ትምህርቶች በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተገለፀ ሲሆን ይህን ለማስፈፀም የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ የትምህርት ዘርፍ ተቋቁሟል።

እውቀትን ወደ ታች በማውረድ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ የ10 አመቱ አንዱ የእቅድ አካል መሆኑንም በ ውይይቱ ላይ ተገልጿል።

Recent News
Follow Us