News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 11, 2021 449 views

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና 565ሺ 255 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ይህም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 96 ከመቶ ነው። 

የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተናግረዋል። 

በ2ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል። 

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም ብለዋል። 

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።

Recent News
Follow Us