News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 06, 2021 1.2K views

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን ይሰጣል

የ2013 ዓመተ ምህረት የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡
የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በሰጡት መግለጫ ከ616 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ አስታውቀዋል፡፡
ለዚህም 16 ሺህ ፋታኝ መምህራን እና 2 ሺህ 112 መፈተኛ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል፡፡
ፈተናው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡
Recent News
Follow Us