News Detail
Oct 06, 2021
848 views
ለትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ዳይሬክተሮች በአመራርነትና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራዎች የተቋቋመው TASFA (Teach And Serve For Africa) ድርጅት ነው ስልጠናውን እየሰጠ ያለው።
ስልጠናው የተቋሙ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በሚመሯቸው ዘርፎች ሁሉ በእውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር እንዲሰጡና የተሻለ አስተዳደር እንዲዘረጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።
ስልጠናው በአመራርነት ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን፣ የተቋም ግንባታ፣ አገልጋይነት፣ ግጭት ማስወገድ፣ የቡድን ስራ፣ የእውቀት ቅንጅት፣ ተወዳዳሪነትና የመሳሰሉትን ያካተተ ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) እንደ ትምህርት ተቋም የተቋሙን አመራሮችና ሰራተኞች አቅም መገንባት ላይ እንሰራለን ብለዋል።
ድርጅቱ ባለፉት አመታት ከ5ሺ 509 በላይ ለሚሆኑ ለመንግስት ሰራተኞች የተለያዩ ስልጠናዎችን ሰጥቷል።