News Detail
Aug 27, 2020
533 views
የ ትምህርት ሚኒስቴር በፊንላንድ መንግስት ይሰጥ የነበረውን ድጋፍ እና ትብብር ሲመሩ ለነበሩት ባለሙያ ሽኝት አካሄደ፡፡
የ ትምህርት ሚኒስቴር በፊንላንድ መንግስት ይሰጥ የነበረውን ቴክኒካል እና የ ገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የ አጋር ድርጅቶች የ ጋራ ትብብርን ሲመሩ ለቆዩት ዶ/ር ሳይ ቫይረን በ ጽህፈት ቤቱ ሽኝት አካሂዷል፡፡
ዶ/ር ሳይ ላለፉት ሶስት አመታት በ ፊንላንድ መንግስት ድጋፍ እየተከናወነ ያለውን የ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ለ ፍትሃዊነት ፕሮጀክት እና የአጋር ድርጅቶች የጋራ ትብብርን ሲመሩ ቆይተዋል፡፡
በሽኝት ስነስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስቴሩ ዶ/ር ኢንጂ. ጌታሁን መኩሪያ ዶ/ር ሳይ በ ትምህርት ዘርፉ ላበረከቱት አስተዋፆ እና ለሰጡት የ ሶስት አመት አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በ ትምህረት ዘርፍ በተለይም ልዩ ፍላጎት እና አካቶ ትምህርት ላይ የ ፊንላንድ መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በቀጣይም የፊንላንድ መንግስት ለ ትምህርት ዘርፉ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ለማጠናከር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡