News Detail

National News
Dec 18, 2020 777 views

ሀገር አቀፍ ሴት የትምህርት አመራሮች የጋራ መድረክ ተመሰረተ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከEducation Development Trust (EDT) እና ከUKaid ጋር በመሆን በትብብር በተዘጋጀ መድረክ ሀገር አቀፍ ሴት የትምህርት አመራሮች የጋራ መድረክ አንዲመሰረት ተደርጓል፡፡

በምስረታው ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ገረመው ሁሉቃ (ፒ ኤች ዲ) እንደገለፁት ሀገር አቀፍ ሴት የትምህርት አመራሮች መድረክን በመመስረት ሴቶች በአመራር ብቃታቸው ለሀገር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የመድረኩ የተመሰረተበት ዋና አላማም በትምህርቱ ዘርፍ ያሉ ሴት መምህራንና አመራሮች ሞዴል ሴት አመራሮችን እንደ ምሳሌ በመውሰድ ወደ አመራርነት ሊያመጣቸው የሚችሉ ብቃትና ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ ውጤታማ የትምህርት ስራ አመራሮች ሆነው እንዲገኙ ማስቻል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በትምህርት መስክ የሚገኙ ሴቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት በዘርፉ ሊመዘገቡ የሚገባቸውን ለውጦች ለማስገንዘብ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ሀገር አቀፍ ጥምረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ጥምረቱ በአሰራር ስርዓት ላይ የሚታየውን ማነቆ ለማለፍና ሴቶችም ያላቸውን አቅም ለመጠቀም እንደሚያግዝም ተገልጿል።

በሀገሪቱ በትምህርት መስክ ሴቶችን በማብቃት ረገድ የተወሰኑ ስራዎች ቢሰሩም ሴቶችን በዘርፉ ወደ አመራርነት ማምጣት የተቻለው 10 በመቶ እንኳን የሚሞላ እንዳልሆነ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

መድረኩ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ እንደሚዘረጋም ተሳቢ ተደርጓል፡፡

Recent News
Follow Us