News Detail
Dec 17, 2020
704 views
የኢትዮጵያና የሩስያ መንግስታት የጋራ ኮሚሽን በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሱ ስምምነቶች ያሉበትን ደረጃ ገመገመ።
የኢትዮጵያና የሩስያ የጋራ ኮሚሽን መሪዎች በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ፣ ቴክኒክ እና የንግድ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) እና በሩስያ ፌደሬሽን የተፈጥሮ ሃብትና የአካባቢ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትርና የፌደራል የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ሃላፊ ኤቫግኒ ኪሰልቭ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል።
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) እና በሩስያ ፌደሬሽን የተፈጥሮ ሃብትና የአካባቢ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትርና የፌደራል የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ሃላፊ ኤቫግኒ ኪሰልቭ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል።ሁለቱ ሚኒስትሮች ጥቅምት 2019 ላይ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሩስያ ሴንት ፒተርስበርግ የተስማሙባቸው ጉዳዮች ያሉበትን ደረጃ ገምግመዋል።
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ኮሚሽኑ የጎላ አስተዋፅኦ ማድረጉ በውይይቱ ተገልፁዋል።
ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የሚያስችላትን የሁለቱን ሀገራት ስምምነት የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማፅደቁን የጋራ ኮሚሽኑ አድንቋል።
በውይይቱ የኮሚሽኑ 8ተኛውን የጋራ ስብስባ 2021 ላይ በአዲስ አበባ ለማድረግ ተስማምተዋል።