News Detail

National News
Jul 26, 2024 1.4K views

መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ 5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ (5 million Ethiopian Coders) የተሰኘ ስልጠና አመቻችቷል።

መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ” የተሰኘ አዲስ የስልጠና እድል አመቻችቷል። ይህ ኢኒሼቲቭ ከአይሲቲ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኮርሶች ጥራቱና በጥልቅ ይዘቶች በሚታወቀው በኦዳሲቲ ፕላትፎርም (Udacity Platform) የፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አርተፊሻል ኢንተለጀንስና ሌሎችም ከአይሲቲ ጋር የተገናኙ ኮርሶችን ከክፍያ ነፃ ማግኘት የሚያስችል ነው።
ተማሪዎች እና መምህራን ያለምንም ወጪ በእነዚህ ኮርሶች በመመዝገብ ይህንን ልዩ የስልጠና እድል መጠቀም የሚችሉ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍና ችሎታቸውን በማጎልበት በአለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ።
በዚህ ስልጠና ተመዝግበውና የትምህርት ይዘቶቹን ተምረው ያጠናቀቁ ተሳታፊዎች በአለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና ያለው እና የስራ እድልን በእጅጉ ሊያሳድግ ከሚችለው Udacity የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር በስልጠናው እንዴት መመዝገብና መሳተፍ እንደሚቻል የሚያሳዩ መመሪያዎችን በጽሁፍና በቪዲዮ አዘጋጅቷል። ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎችና መምህራን ይሄንን በበዙ ክፍያ ይሰጥ የነበረን ስልጠና መመሪያውን ተከትሎ ብቻ በመመዝገብ በነጻ መሰልጠን ትችላላችሁ።
የመመሪያውን የቪዲዮ ሊንክ https://youtu.be/-zSmhhD5qE4 ላይ በመግባት መመልከት የምትችሉ ሲሆን በምስል የተደገፈውን መመሪያም ከዚህ ፖስት ጋር አጋርተናል።
ይሄንን ጠቃሚና ነጻ የስልጠና እድል ፍላጎቱ ላላቸውና የትምህርት ዝግጅታቸው ከዚህ ስልጠና ጋር ለሚገናኝ ጓደኞቻችሁ፣ ወዳጅ ፣ ቤተሰባችሁ እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራን በማጋራት ተጨቃሚ እንዲሆኑ አድርጉ።
Recent News
Follow Us