News Detail
Apr 29, 2024
1.7K views
በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ከ50 ሺ በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በክረምት ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገለፀ።
በዚህ ዓመት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመምህራን የክረምት ስልጠና ከ50 ሺ በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና ይሠጣል ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህ የሚሠጠው የክረምት ስልጠና አሁን እያስተማሩ ያሉ መምህራን በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘትና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ ክህሎት እንዲይዙ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም መምህራን በሚያገኙት ስልጠና በሚያስተምሩት ትምህርት ላይ ትምህርቱን በበቂ ማስተማር የሚያስችላቸው ክህሎት ያገኛሉም ብለዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው ይህ የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የክረምት ስልጠና የተሳካ እንዲሆን ክልሎች ተባብረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የመምህራን የክረምት ስልጠና አተገባበር ስትራቴጂ በመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱም የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ለመምህራን የሚሰጠው ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩት ትምህርት ይዘትና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጠቃሚ መሆኑንም አንስተዋል
Recent News
Sep 10, 2024
Sep 17, 2024
Sep 04, 2024
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
Aug 30, 2024